መጋቢት 24 ቀን 2010 ዓ.ም ኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን ሲመኙት የነበረው የዲሞክራሲ ህልም እውን የሆነበት ነው ሲሉ የትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ሚኒስትር አለሙ ስሜ (ዶ/ር) ተናገሩ።
የመጋቢት የቀጣዩ አርበኝነት ጅማሮ ማብሰሪያ መርሐ-ግብር በትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ሚኒስቴር እየተካሄደ ይገኛል።
በመርሐ-ግብሩ ሚኒስትሩ፣ የኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ብልፅግና እውን የሆነበት፣ የኢትዮጵያውያን ተጠቃሚነትና ንቁ ተሳታፊነት የተረጋገጠበት ምክንያት ዘመን ተሻጋሪና ነገን ታሳቢ ያደረጉ ተግባራት በመከናዎናቸው ነው ብለዋል።
በትክክለኛ አቅጣጫ የሚመራና ሀሳብን ከተግባር፣ አካታችነትን ከፍትሀዊነት ጋር በማዋሀድ የሚመራ መሪ ስላለን የዛሬይቱ ኢትዮጵያ ልትመሰረት ችላለች ብለዋል።
ሀሳብ ያለውን ጉልበት ለመመልከት አዲስ አበባ ዛሬ ያላትን መልክ መመልከት ምስክር ነው ያሉት ሚኒስትሩ፣ ይህም ያለፉትን ዓመታት ቁጭትና የማንቀላፋት ዘመን ማካካሻ ስለመሆኑ አንስተዋል።
ከዚህ ባሻገር እየተሰሩ ባሉ ዲፕሎማሲያዊ ተግባራት ኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤት ትሆናለች በማለት አለሙ ስሜ (ዶ/ር) ተናግረዋል።
“ትናንት፣ ዛሬና ነገን ለኢትዮጵያ ልዕልና” በሚል መሪ ሀሳብ ያለፉት ሰባት የለውጥ ዓመታት በትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ሚኒስቴር እየተከበረ ይገኛል።
በመርሀ ግብሩ የትራንስፖርት ሚኒስትር አለሙ ስሜ (ዶ/ር)ን ጨምሮ ሌሎች ባለድርሻ አካላት እየተሳተፉ ይገኛል።
በንጉሱ በቃሉ