AMN – ታኅሣሥ 29/2017 ዓ.ም
ማዕድ ማጋራት የአብሮነት’ የመተሳሰብ እና የፍቅር መገለጫ ነው ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ሀላፊ አቶ አብረሃም ታደሰ ተናገሩ፡፡
የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ከአዲስ አበባ ትረስት ፈንድ ጽ/ቤት ከመሬት ይዞታ ና ምዝገባ ኤጀንሲ ጋር በመተባበር ለችግረኛ ወገኖች የገና በዓልን አስመልክቶ የምሳ ግብዣ ፕሮግራም አካሂዷል።
በተስፋ ብርሃን ቁጥር 2 የምገባ ማዕከል በተደረገው የምሳ ግብዣ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ሀላፊ አቶ አብረሃም ታደሰ ባስተላለፉት መልዕክት በዓላትን ስናከብር ድጋፍ ከሚያስፈልጋቸው ወገኖችጋር አብሮ በመሆን ሊሆን ይገባል ብለዋል፡፡
ማዕድ ማጋራት አብሮነትን በማጠናከር ነባሩን የመተጋገዝ ባህል ያጠነክራልም ሲሉ አመልክተዋል፡፡
ማዕድ ማጋራት የአብሮነት’ የመተሳሰብ እና የፍቅር መገለጫ ነው ሲሉ ተናግረዋል ።
የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ አለምፀሃይ ሺፈራው መንግስት ሰው ተኮር ስራዎችን በማከናወን የሁሉንም ማህበረሰብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትኩረት እየተሰራ ስለመሆኑ አውስተው የእነዚህ ተግባራት አካል በሆነው የምገባ ፕሮግራም በክፍለ ከተማው ተጠቃሚ የሆኑ ወገኖች በበዓላት ወቅት በደስታ እንዲያከብሩ አመራሩ አብሮነቱን የሚገልፅበት ነው ብለዋል።

በሀገር አቀፍና በአዲስ አበባ ከተማ በርካታ ዜጎች የምገባ መርሃ ግብር ተጠቃሚ ሆነዋል ብለዋል።
በዓላትን በጋራ ማክበር አብሮነትን የሚያጎላ ነው ሲሉ ጠቅሰዋል።
በከተማ አስተዳደሩ እየተሰሩ ያሉ የልማት ስራዎችን ለዜጎች ምቹና ተስማሚ በማድረግ የዜጎች ተጠቃሚነት የታየበት ነው ብለዋል።
አስተያየታቸውን ለኤ ኤም ኤን የሰጡ ማዕዱን የተጋሩ ዜጎች ”በዓሉን በደመቀ ሁኔታ አንድላይ ማክበራቸው እንዳስደሰታቸው ተናግረው ለተደረገላቸው ነገር ሁሉ አመሥግነዋል ።
በመሀመድኑር አሊ