“እርሶ በርግጥ ከእስራኤል ጎን ወግነው ይዋጉ ይሆን?” ተብለው የተጠየቁት የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አወዛጋቢ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡
” አዎ እንደዛ ላደርግ እችላሁ ወይም አላደርግም ይሆናል” ብለዋል ፡፡
አክለውም እኔ የማደርገውን ነገር ማንም ሰው ሊያውቅ አይችልም ያሉት ፕሬዚዳንቱ ኢራን በከባድ ጭንቀት ውስጥ ስለገባች ወደ ድርድር እንደምትመጣ መናገር እችላለሁ ሲሉ መደመጣቸዉን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
ቀደም ሲል ትራምፕ ኢራን ሆይ እጅሽን ስጪ ማለታቸውን ተከትሎ የኢራኑ መንፈሳዊ መሪ ኢራን ፈፅሞ እጅ አትሰጥም ይልቁን አሜሪካ ሆይ ሊደርስብሽ ከሚችል የማይጠገን ጉዳት እራስሽን ጠብቂ ማለታቸው ይታወሳል፡፡