AMN – የካቲት 11/2017 ዓ.ም
ኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽንን የሦስት ዓመት የስራ አፈፃፀምን አዳምጧል፡፡
ኮሚሽኑ በሚቀጥለው የካቲት 14 የተፈቀደለትን የሶስት ዓመት ጊዜ በማጠናቀቁ እና ቀሪ ስራዎችን በትጋት ለመስራት ለተጨማሪ አንድ አመት እንዲራዘም ተጠይቋል።
ጥያቄውን ያቀረቡት የዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ እውነቱ አለን፣ ኮሚሽኑ ቀሪ ስራዎችን በትጋት ይፈፅም ዘንድ ተጨማሪ አንድ ዓመት ያስፈልገዋል ብለዋል።
የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን ባካሄደው 1ኛ አስቸኳይ ጉባዔ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የሦስት ዓመት የስራ አፈፃፀምን በማዳመጠ የቀሩ ስራዎችን ለማጠናቀቅ የተጠየቀውን አንድ አመት በ3 ተቃውሞ በአብላጫ ድምጽ አጽድቋል።
በሄለን ጀንበሬ