ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ከቻይና ሕዝብ የፖለቲካ ምክክር ጉባኤ ብሔራዊ ኮሚቴ ምክትል ሊቀ መንበር እና የቻይና የኢንዱስትሪና የንግድ ፌዴሬሽን ሊቀመንበር ጋር ተወያዩ

You are currently viewing ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ከቻይና ሕዝብ የፖለቲካ ምክክር ጉባኤ ብሔራዊ ኮሚቴ ምክትል ሊቀ መንበር እና የቻይና የኢንዱስትሪና የንግድ ፌዴሬሽን ሊቀመንበር ጋር ተወያዩ

AMN – ሚያዝያ 16/2017

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ የቻይና ሕዝብ የፖለቲካ ምክክር ጉባኤ ብሔራዊ ኮሚቴ ምክትል ሊቀ መንበር እና የቻይና የኢንዱስትሪና የንግድ ፌዴሬሽን ሊቀመንበር ጋኦ ዩንሎንግ ጋር ተወያይተዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት የቻይና ሕዝብ የፖለቲካ ምክክር ጉባኤ ብሔራዊ ኮሚቴ ምክትል ሊቀ መንበር እና የቻይና የኢንዱስትሪና የንግድ ፌዴሬሽን ሊቀመንበር ጋኦ ዩንሎንግ እና የልዑክ ቡድናቸው ወደ ኢትዮጵያ እንኳን በደኅና መጡ ብለዋል፡፡

በኢትዮጵያ እና በቻይና መካከል ያለውን የኢንቨስትመንት፣ የኢኮኖሚ ልማት እና የንግድ ትብብርን ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ከሊቀ መንበሩ ጋር ውይይት አካሂደናል ሲሉም ገልጸዋል፡፡

ምክትል ሊቀመንበር ጋኦ ዩንሎንግ ኢትዮጵያ እያከናወነች ያለችውን የልማት እንቅስቃሴ ማድነቃቸውንም ገልጸዋል፡፡

በተለይም መዲናችን አዲስ አበባ በእጅጉ እንደተለወጠችና ባዩት ስኬታማ ሥራ መደነቃቸውን እንደተናገሩም አክለዋል፡፡

ኢትዮጵያ በኢንቨስትመንቱ ዘርፍ ለቻይናውያን ባለሀብቶች ምቹ መሆኗን እና በሁኔታዎች የማይቀያየር የሁለቱ ሀገራት ስትራቴጂካዊ አጋርነት በኢኮኖሚው መስክም ይበልጥ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ተግባብተናል ብለዋል ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልዕክታቸው።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review