AMN – የካቲት 14/2017 ዓ.ም
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ለ3ኛ ጊዜ በሚካሔደው የG-25 የአፍሪካ ቡና አምራች ሀገራት ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ ታንዛኒያ ዳሬ ሰላም ከተማ ገብተዋል።
አቶ ተመስገን በዳሬ ሰላም ለ3ኛ ጊዜ በሚካሔደው የG-25 የአፍሪካ ቡና አምራች ሐገራት ጉባዔ ላይ እንደሚካፈሉ ይጠበቃል።
የአህጉሩ ቀዳሚ የቡና አምራች የሆነችው ኢትዮጵያን ጨምሮ 25 የአፍሪካ ቡና አምራች ሀገራት በጉባዔው እንደሚሳተፉ ኢዜአ ዘግቧል።
”የአፍሪካ የቡና ኢንዱስትሪን በማነቃቃት ለወጣቶች የሥራ ዕድሎችን መክፈት” በሚል መሪ ቃል በሚካሔደው ጉባዔ ዘርፉን ለማነቃቃትና ሰፊ የስራ ዕድል ለመፍጠር የሚያስችሉ ውይይቶች እንደሚካሔዱ ይጠበቃል።