
AMN – ግንቦት 18/2017 ዓ.ም
የሞስኮን መጠነሰፊ የድሮን እና የሚሳኤሎች ጥቃት ተከትሎ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ቭላድሚር ፑቲንን ድርጊት አውግዘዋል።
ከፕሬዝዳንት ፑቲኒን በበርካታ የትብብር መስኮች በጋራ ለመስራት ብዙ ጥረቶች እየተደረጉ በሚገኙበት በአሁን ወቅት የሰላሙን ጥረት ወደ ኋላ የሚጎትት ነው በማለት ኮንነዋል
የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎድሚር ዜሌንስኪ በበኩላቸው የዋሺንግተን ዝምታ ፑቲን ይህን ጥቃት እንዲፈጽሙ ያደረጋቸው በማለት ድርጊቱን አውግዘዋል
በዚህም አሜሪካ በሩሲያ ላይ ጠንከር ያለ ማእቀብ በመጣል ጫና ማሳደር እንደሚገባት አሳስበዋል።
የፈረንጆቹ 2022 ዓመት ጀምሮ በአንድ ምሽት ከተፈጸሙ ጥቃቶች ሁሉ የትናንት ምሽቱ የ367 የድሮን እና የሚሳኤል ጥቃት ከፍተኛ ቁጥር ያስመዘገበ መሆኑን በመግለጽ በጥቃቱም 12 ሰዎች እንደተገደሉ እና ቁጥራቸው በውል የማይታወቁት መቁሰላቸውን ተገልጿል።
በሌላ በኩል ትራምፕ ለዜሌንስኪም ከክፉ ንግግር ሊቆጠቡ ይገባል በማለት ጠንከር ያለ መልዕክት ሰንዝረዋል
በ2014 የያዘችውን መሬት ጨምሮ ሞስኮ እስካሁን የዩክሬንን 20 በመቶ ግዛት መቆጣተሯን ቢቢሲ በዘገባው አስነብቧል።
በወርቅነህ አቢዮ