“ሪፎርም እና ጠቅላይ ሚኒስትሩ” በሚል ርዕስ ተጽፎ የተዘጋጀው መፅሐፍ ተመረቀ

You are currently viewing “ሪፎርም እና ጠቅላይ ሚኒስትሩ” በሚል ርዕስ ተጽፎ የተዘጋጀው መፅሐፍ ተመረቀ

AMN – ጥቅምት 24/2017 ዓ.ም

“ሪፎርም እና ጠቅላይ ሚኒስትሩ” በሚል ርዕስ በአቶ ኢብሳ ነገዎ ተጽፎ የተዘጋጀው መፅሐፍ በአዲስ አበባ ተመርቋል።

በምርቃት መርሐ-ግብሩ የጸሐፊው የትግል ጓዶች እና ከፍተኛ የመንግስት አመራሮችን ጨምሮ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

ጸሐፊው በኦሮሞ የትግል እንቅስቃሴ ውስጥ ያበረከቱት አስተዋጽኦ እና ትግሉ ከግብ ይደርስ ዘንድ የከፈሉት መሰዋዕትነት እንዲሁም የዓላማ ጽናት አና ለህዝቡ ያላቸው ፍቅር የላቀ ስለመሆኑም በመድረኩ ተነስቷል።

አቶ ኢብሳ ነገዎ ይህን መጸሀፍ ለመጻፍ ለበርካታ ጊዜያት ሲያልሙ እንደነበር ተናግረዋል።

በመራር ትግል የተገኘው ነጻነት አስፈላጊ ነው፣ መጽሃፉ የተጻፈውም ይህንን ለውጥ ለመደገፍ ነው ሲሉም አክለዋል።

በተጨማሪም በሀገር አቀፍ ደረጃ የተጀመረውን ሪፎርም መደገፍ ሌላኛው የመፅሐፉ ዓላማ መሆኑ ተመላክቷል።

በዛሬው ዕለት ለምረቃ የበቃው መፅሐፍ በአማርኛ እና በኦሮምኛ ቋንቋዎች ተፅፎ መዘጋጀቱም ተገልጿል፡፡

በሀብታሙ ሙለታ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review