ሰላም እና የሀገር አንድነት ልዩነቶችን ለመፍታት በሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ውስጥ ሊታለፉ የማይገቡ ቀይ መስመሮች መሆናቸው ተገለጸ

You are currently viewing ሰላም እና የሀገር አንድነት ልዩነቶችን ለመፍታት በሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ውስጥ ሊታለፉ የማይገቡ ቀይ መስመሮች መሆናቸው ተገለጸ

AMN – ግንቦት 13/2017 ዓ.ም

የፕሪቶሪያ የሰላም ንግግር ዋና ተደራዳሪ የነበሩት እና የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ዳይሬክተር ጀኔራል አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን የፕሪቶሪያውን የሰላም ንግግር አስመልክቶ ከመገናኛ ብዙሃን ጋር በነበራቸዉ ቆይታ ልዩነቶች መስተናገድ ያለባቸው ከሀገር አንድነት እና ህልውና በመለስ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ሰላም እና የሀገር አንድነት ልዩነቶችን ለመፍታት በሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ውስጥ ሊታለፉ የማይገቡ ቀይ መስመሮች መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

ማንኛውም አካል ሀገር በየጊዜው ከሚለዋወጡ መንግስታት አቋም እና ፍላጎቶች እንደምትበልጥ በማስተዋል ፤ የሐሳብ ልዩነቱ ከኢትዮጵያ ጥቅም እና ሉዓላዊነት በተቃራኒ ሊያሰልፈው እንደማይገባ አስገንዝበዋል፡፡

ሁሉም ዜጋ ‘ሀገር’ የሚለውን ትልቁን ምስል አጉልቶ ማየት እንዲችል ፤ ገዢ ብሔራዊ ትርክትን ማጎልበት እንደሚገባም አበክረዋል፡፡

አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ሁሉም ጥያቄዎች ከኢትዮጵያዊነት ወለል በታች ሳይወርዱ መመለስ እንዳለባቸውም ከኢዜአ ጋር በነበራቸው ቆይታ አመላክተዋል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review