ሳምሶን መኮንን (ዶ/ር) የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ሆነው ተሾሙ

AMN – ጥር 6/2017 ዓ.ም

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 15ኛ መደበኛ ጉባዔውን አድርጓል።

ምክር ቤቱ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሀን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሹመትን አስመልክቶ የቀረበለትን የውሳኔ ሀሳብ መርምሮ በአንድ ድምፀ ተአቅቦ በአብላጫ ድምፅ አፅድቋል።

በዚሁ መሠረት ሳምሶን መኮንን (ዶ/ር) የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ሆነው መሾማቸውን የምክር ቤቱ መረጃ ያሳያል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review