ስምምነቱ ከፍተኛ ውጤት እየተመዘገበበት ለሚገኘው የግብርና ሴክተር ተጨማሪ አቅም ከመገንባት ባለፈ ለዜጎች የስራ ዕድል የሚፈጥር ነው-ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

You are currently viewing ስምምነቱ ከፍተኛ ውጤት እየተመዘገበበት ለሚገኘው የግብርና ሴክተር ተጨማሪ አቅም ከመገንባት ባለፈ ለዜጎች የስራ ዕድል የሚፈጥር ነው-ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

AMN-የካቲት 10/2017 ዓ.ም

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ፣ የግብርና ስራዎች ኮርፖሬሽን እና አሴት ግሪን ኃ/የ/የ/ማህበር የኢትዮጵያና ዩናይትድ ኪንግደምን የጋራ የንግድ ትብብር የሚያጠናክር ኢንቨስትመንት ተፈራርመዋል፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ስምምነቱን አስመልክተው በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባጋሩት መልዕክት፣ ይህ የዩናይትድ ኪንግደም አቻቸው አንጄላ ሬይነር በተገኙበት የተከናወነው የአክሲዮን ባለድርሻ ስምምነት ኢትዮጵያና ዩናይትድ ኪንግደም በግብርናው ዘርፍ የተቀናጀ የሰብል ልማት እና የወተት ተዋጽኦ ምርት እና ንግድ እንዲያከናውኑ የሚረዳ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ስምምነቱ ከፍተኛ ውጤት እየተመዘገበበት ለሚገኘው የግብርና ሴክተር ተጨማሪ አቅም ከመገንባት ባለፈ ለዜጎች የስራ ዕድል የሚፈጥር መሆኑንም አውስተዋል፡፡

በተጨማሪም ስምምነቱ ዘመናዊ እና አስተማማኝ የግብርና ስራ እንዲከወን እንዲሁም የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንትን የሚያበረታታ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review