ስንፍናን የሚጠየፍ ትውልድ መፍጠር የሀገር ሉዓላዊነት ጉዳይ መሆኑን ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ተናገሩ

You are currently viewing ስንፍናን የሚጠየፍ ትውልድ መፍጠር የሀገር ሉዓላዊነት ጉዳይ መሆኑን ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ተናገሩ

AMN- ሰኔ 12/2017 ዓ.ም

“ስንፍናን የሚጠየፍ ትውልድ መፍጠር የሀገር ሉዓላዊነት ጉዳይ ነው” ሲሉ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ተናገሩ፡፡

“የሥራ ባህልና ምርታማነት ለሀገር ሉዓላዊነት” በሚል መሪ ሀሳብ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ጋር በትብብር ያዘጋጀው የምክክር መድረክ እየተካሄደ ይገኛል።

መድረኩ የሥራ ባህልን በማሻሻልና ምርታማነትን በማሳደግ የሀገርን ሉዓላዊነት ለማስጠበቅ እየተደረገ በሚገኘው እንቅስቃሴ ዙሪያ ግንዛቤ ለመፍጠር ያለመ መሆኑ ተመላክቷል።

ከዓለም ነባራዊ ሁኔታ ጋር እኩል መራመድ የግድ እንደሚል ያነሱት የስራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል፣ ለእዚህም ምርትና ምርታማነት ላይ መስራት እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።

ምርትና ምርታማነት የሀገር ሉዓላዊነት ጉዳይ መሆኑን አፅንዖት በመስጠትም ስንፍናን የሚጠየፍ ትውልድ መፍጠር ላይ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደሚያስፈልግ ገልፀዋል።

በመድረኩ ለውይይት መነሻ የሚሆን የሥራ ባህልና ምርታማነት ከተለያዩ አውዶች የተቃኘበት ፅሁፍ ቀርቦ ውይይት እየተደረገ ይገኛል፡፡

በመድረኩ ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች፣ ስራ ፈጣሪዎች እና ምሁራን ታድመዋል።

በመቅደስ ደምስ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review