በ28ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ቼልሲ ተከታታይ የፕሪሚየር ሊግ ድሉን አስመዘገበ

You are currently viewing በ28ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ቼልሲ ተከታታይ የፕሪሚየር ሊግ ድሉን አስመዘገበ

AMN-የካቲት 30/2017 ዓ.ም

የ 28ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬም ቀጥሎ ሲደርግ ቼልሲ ተከታታይ የፕሪሚየር ሊግ ድሉን አስመዝግቧል።

በስታምፎርድ ብሪጅ ሌስተር ሲቲን ያስተናገደው ቼልሲ 1ለ0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።

ስፔናዊው የግራ ተመላላሽ ማርክ ኩኩሬላ ደግሞ ብቸኛዋን የጨዋታ ግብ በ60 ኛው ደቂቃ ላይ ከመረብ አሳርፏል።

ሰማያዊዎቹ ማሸነፋቸውን ተከትሎ ነጥባቸውን 49 በማድረስ 4ኛ ደረጀ ላይ ሲቀመጡ 7ኛ ተከታታይ ሽንፈታቸውን ያስተናገዱት ሌስተር ሲቲዎች በአንጻሩ በ17 ነጥብ በወራጅ ቀጠናው 19ኛ ላይ ተቀምጠዋል።

በሌላ የሊጉ ጨዋታ ቶተንሃም ሆትፐርስና በርንማውዝ ነጥብ ተጋርተዋል።

2 አቻ በተጠናቀቀው ጨዋታ በርንማውዝ በማርከስ ታቬርነርና ኢቫኒልሰን አማካኝነት ቀዳሚ መሆን ቢችሉም ስፐርሶች ፔፕ ሳር በጨዋታና ሰን ሁንግ ሚን በፍፁም ቅጣት ምት ባስቆጠሯቸው ጎሎች አቻ ተለይተዋል።

ውጤቱን ተከትሎም ቶተንሃም በ34 ነጥብ 13ኛ ላይ ሲቀመጥ በርንማውዝ በ44 ነጥብ 8ኛ ላይ ተቀምጧል።

በዘላለም አብይ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review