በ29ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ መርሀ ግብር አርሰናል እና ፉልሀም አሸነፉ፡፡

You are currently viewing በ29ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ መርሀ ግብር አርሰናል እና ፉልሀም አሸነፉ፡፡

AMN-መጋቢት 7/2017 ዓ.ም

በኤምሬትስ የተደረገዉ የአርሰናል እና የቼልሲ ጨዋታ በአርሰናል 1ለ0 አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡

ሚኬል ሜሪኖ 20ኛዉ ደቂቃ ላይ ያስቆጠራት ግብ መድፈኞቹን አሸናፊ ያደረገች ስትሆን በጨዋታዉ ብልጫ ወስደዋል፡፡

አርሰናል የዛሬዉን ጨዋታ ጨምሮ ያለፉትን 7 ጨዋታዎች በቼልሲ ያልተሸነፈ ሲሆን ከዚህ በፊት ከ1999 እስከ 2005 የዉድድር አመት ያልተሸነፈበት ደግሞ ተጠቃሽ ነበር፡፡

ቶተነሀምን በሜዳዉ ያስተናገደዉ ፉልሀም ደግሞ 2ለ0 በሆነ ዉጤት አሸንፏል፡፡

78ኛዉ ደቂቃ ድረስ ግብ ሳይቆጠረብት በዘለቀዉ ጨዋታ ሮደሪጎ ሙኔዝ እና ረያን ሴሴኞን አከታትለዉ ባስቆጠሯቸዉ ግቦች የአሰልጣኝ ማርኮ ሲልቫዉ ቡድን 3 ነጥብ አሳክቶ ወጥቷል፡፡

የመርሀ ግብሩ ምሽት 4 ሰአት ላይ ሌይስተር ሲቲ ማንችስተር ዩናይትድን በሚያስተናግድበት ጨዋታ ይጠናቀቃል፡፡

በአልማዝ ከዳነ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review