
AMN-ኅዳር 19/2017 ዓ.ም
በሃይማኖት ተቋማት መካከል የሚስተዋለው ትብብር የሀገርን ዘላቂ ሰላም በማረጋገጥ በአማኒያን መካከል ይበልጥ ትስስር እንዲጠናከር የሚደርግ ነው ሲሉ የሀይማኖት አባቶች ገለጹ፡፡
የአዲስ አበባ የሐይማኖት ተቋማት ጉባኤ አባላት የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤትን ጎብኝተዋል።
የሀይማኖት ተቋማት ህበረተሰቡ ውስጥ የአንድነት እሴቶት እንዲጎለብት የማድረግ ሃላፊነት አለባቸው እንዳለባቸው የሀይማት አባቶቹ በጉብኝቱ ወቅት ተናግረዋል፡፡
በዚህም ለዓመታት ህዝብ ለህዝብ እንዲከባበር በስነምግባር ጭምር ታንጾ እንዲኖር ለማድረግ በተለያዩ አደረጃጀቶች በመዋቀር ጭምር ሚናቸውን ሲወጡ ቆይተዋል ተብሏል፡፡
አሁንም በመወጣት ላይ እንደሚገኙ ተገልጿል፡፡
የዚሁ አንድ አካል የሆነው የአዲስ አበባ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤም “የሐይማኖት ተቋማት ትብብርና አብሮነትን ማጎልበት ለዘላቂ ሰላም” በሚል መሪ ሃሳብ የጉባኤው የቦርድ አመራሮች የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤትን ጎብኝተዋል።
የሃይማኖት ተቋማት በትብብር መስራት አማኙ የሚያነሳቸውን ጥያቄዎች በጋራ ምላሽ ለመስጠት ትልቅ እቅም መሆኑን የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሼህ ሱልጣን አማን ኤባ ተናግረዋል፡፡
የልምድ ልውውጥ መደረጉ በአማኒያን መካከል ይበልጥ ትስስር እንዲጠናከር ያደርጋልም ብለዋል።
በጉብኝት መርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ ዋና ፀሀፊ መጋቢ ታምራት አበጋዝ በበኩላቸው በጉብኝቱ ኢትዮጵያ ሀይማኖቶች በጋራ የኖሩባት ሀገር መሆኗን ያዩበትና ይህንን ለትውልድ ማሻገር ከሀይማኖት አባቶች እንደሚጠበቅ ትምህርት የወሰዱበት ስለመሆኑ አንስተዋል።
የአዲስ አበባ የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ በተቋማቱ መካከል ያለውን ትብብር ለማጠናከር በትኩረት እየተሰራ ነው ያሉት ዋና ፀሀፊው በተለይ በሰላም ጉዳይ በትብብር መስራት እንደሚገባ አንስተዋል፡፡
ጉብኝቱ በሀይማኖት ተቋማት መካከል ያለውን ትብብር በማጠናከር ሃላፊነታቸውን ይበልጥ እንዲወጡ አጋዥ ከመሆኑ ባለፈ አብሮነት እንዲጎለብት በር የከፈተ መሆኑን የሀይማት አባቶቹ አመልክተዋል፡፡
በመሀመድኑር አሊ