በህክምና መሳሪያዎች አቅርቦት ፤ ተያያዥ ሰብአዊ እና የልማት ድጋፎች ላይ በጋራ ለመስራት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ተፈረመ

You are currently viewing በህክምና መሳሪያዎች አቅርቦት ፤ ተያያዥ ሰብአዊ እና የልማት ድጋፎች ላይ በጋራ ለመስራት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ተፈረመ

AMN – ሚያዝያ 17/2017

ጄኔቫ የሚገኘዉ አለም አቀፍ የውሃ፣ አካባቢ እና ጤና ኢንስቲትዩት ሂውማን ብሪጅ ከተሰኘ መንግስታዊ ካልሆነ ተቋም ጋር በመተባበር በህክምና መሳሪያዎች አቅርቦት ፤ በተያያዥ ሰብአዊ እና የልማት ድጋፎች ላይ በጋራ ለመስራት ተስማሙ፡፡

አክሺን ፎር ዘ ኒዲ የተሰኘ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት በኢጋድ አባል ሀገራት ተሳትፎ እና ከአለም አቀፍ የውሃ፣ አካባቢ እና ጤና ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር በኢትዮጵያ በውሃ፣ አካባቢ እና ጤና ዙሪያ የማማከር ስራ መጀመሩን አስታዉቋል፡፡

የድርጅቱ ማኔጂንግ ዳይሬክተር ሳሊሁ ሱልጣን ሂዉማን ብሪጅ ከአሁን ቀደም ለነጌሌ ሆስፒልና ለገጠራማ አካባቢዎች በ40 ሚሊዮን ብር የሚገመቱ የህክምና ቁሳቁሶችን ድጋፍ ማድረጉን ተናግረዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ ለነጌሌ ሆስፒልና ለገጠራማ አካባቢዎች 80 ሚሊዮን ብር የሚያወጡ ተጨማሪ የህክምና ቁሳቁሶችን ድጋፍ ለማድረግ መስማማቱን ተናግረዋል፡፡

በመግባቢያ ስምምነቱ ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳምሶን ቢራቱ ድርጅቶቹ በጤና፣ በአካባቢ ንጽህና እና በሰብአዊ ምላሽ ላይ እያደረጉ ላለዉ ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

የዉሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር አስፋዉ ዲንጋሞ በበኩላቸዉ ሂውማን ብሪጅ ለችግር ተጋላጭ ለሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን ለመርዳት ለነጌሌ ሆስፒታል ላደረገዉ የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review