በሌማት ትሩፋት እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ስራዎች ገበያን ከማረጋጋት ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከቱ መሆናቸው ተገለጸ

You are currently viewing በሌማት ትሩፋት እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ስራዎች ገበያን ከማረጋጋት ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከቱ መሆናቸው ተገለጸ

AMN – መጋቢት 24/2017 ዓ.ም

በሌማት ትሩፋት እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ስራዎች ገበያን በማረጋጋት ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያደረጉ መሆናቸውን የሐረሪ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር እና የክልሉ ግብርና ልማት ቢሮ ሀላፊ ወ/ሮ ሮዛ ኡመር ገለጹ።

በልማቱ በተለይም የማር፣ የዶሮ፣ የአሳ እና የወተት ምርቶች ከፍተኛ ትኩረት ተሰቷቸው እየተሰራ መሆኑንም ኃላፊዋ ገልጸዋል።

በእነዚህ ስራዎች በትንሽ መሬት ላይ ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ መቻሉን የገለጹት ኃላፊዋ፣ በአመት ሶስት ጊዜ ማምረት መቻሉንም ተናግረዋል።

የሌማት ትሩፋቱ ለወጣቶች እና ለሴቶች የስራ እድል እንዲመቻችላቸው እና ተጠቃሚ እንዲሆኑ አስችሏል ያሉት የቢሮ ሀላፊዋ፣ በተለይም የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ብድር እንዲመቻችላቸው በማድረግ ተጠቃሚነታቸው እየተረጋገጠ መሆኑንም ገልጸዋል።

በሌማት ትሩፋት የልማት ስራዎች የተሰማሩ ዜጎች በበኩላቸው፣ በዘርፉ በተፈጠረላቸው እድል ተጠቃሚ መሆናቸውን ተናግረዋል።

በሀብታሙ ሙለታ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review