በመዲናዋ እየተከናወነ ያለው የወንዞች ዳርቻ ልማት ከተማዋን አዲስ ገጽታ የሚያላብሳት እና ለነዋሪዎች ምቹ የመኖሪያ አካባቢ የሚፈጥር ነው-የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አባላት

You are currently viewing በመዲናዋ እየተከናወነ ያለው የወንዞች ዳርቻ ልማት ከተማዋን አዲስ ገጽታ የሚያላብሳት እና ለነዋሪዎች ምቹ የመኖሪያ አካባቢ የሚፈጥር ነው-የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አባላት

AMN-የካቲት 10/2017 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አባላት በከተማዋ እየተከናወኑ ያሉ የልማት ስራዎች ጎብኝተዋል፡፡

በከተማዋ እየተከናወነ ያለው የወንዞች ዳርቻ ልማት ከተማዋን አዲስ ገጽታ የሚያላብሳት ፣ለነዋሪዎች ምቹ ሁኔታን የሚፈጥር እና ለቀጣዩ ትወልድ መሰረት የሚጥል ተግባር መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በከተማዋ እየተከናወኑ ያሉ የልማት ስራዎች የነዋሪዎችን ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጡ መሆናቸውን የምክር ቤት አባላት ገልጸዋል፡፡

ከእንጦጦ እስከ ፒኮክ ያለውን የወንዞች ዳርቻ ልማት የሚያስተባብሩት የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ጥላሁን ወርቁ፣ ልማቱ የስራ እድልን የሚፈጥሩ መሰረተ ልማቶችን እና ሌሎች ፕሮጀክቶችን አካቶ እየተከናወነ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡

ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ የተለያዩ ፓርኮችን እና በከተማዋ የተከናወኑ ፕሮጀክቶችን በማስተሳሰር ለከተማዋ ሌላ ወብት እና አዲስ ገጽታን የሚያላብስ መሆኑንም አቶ ጥላሁን ተናግረዋል፡፡

በቴዎድሮስ ይሳ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review