በመዲናዋ ውስብስብ የሆኑ ወንጀሎችን በቁጥጥር ስር ማዋል መቻሉን የአዲስ አበባ ፓሊስ አስታወቀ Post published:May 7, 2025 Post category:መልካም አስተዳደር AMN – ሚያዝያ 29/2017 በመዲናዋ ሲያጋጥሙ የነበሩ ውስብስብ የሆኑ ወንጀሎችን በቁጥጥር ስር ማዋል መቻሉን የአዲስ አበባ ፓሊስ አስታውቋል፡፡ በመዲናዋ በመቀናጀት በተሰሩ ስራዎች በአደባባይ የተከበሩ በዓላት እና ኮንፈረንሶች ያለምንም ችግር መከናወናቸውን የአዲስ አበባ ፓሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ጌቱ አርጋው ተናግረዋል። ለስራ ምቹ የሆነ፣ ተወዳዳሪና ደረጃውን የሚመጥን ተቋም የመገንባት ስራ ሰላምን ከማስፈን ጎን ለጎን ስለመከናወኑም ኮሚሽነር ጌቱ አመላክተዋል፡፡ የማህበረሰቡን ሰብዓዊ መብቶች የጠበቀ ህጋዊና አስተዳደራዊ አገልግሎት የመስጠት ስራ በአዲስ አበባ ፓሊስ የተከናወነ እና እየተከናወነ ያለ ተግባር መሆኑም ተመላክቷል፡፡ ከአፍሪካ አምስት ከተሞች የአዲስ አበባ ፓሊስን በአገልግሎት አሰጣጡ ተጠቃሽ ለማድረግ በቴክኖሎጅ የታገዘ ተቋም መገንባት ላይ በትኩረት ስለመሰራቱ ተጠቅሷል። አዲስ አበባን ከወንጀልና ከፀጥታ ስጋት የፀዳች ከተማ ለማድረግ ተቋሙ፣ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ባከናወናቸው ተግባራት ላይ ከሁሉም ክፍለ ከተሞች ከተውጣጡ ባለድርሻ አካላት ጋር እየመከረ ይገኛሉ። በንጉሱ በቃሉ 0 Reviews ( 0 out of 0 ) Write a Review Submit Review You Might Also Like በመዲናዋ የመንጃ ፈቃድ ዕድሳት አገልግሎት በመታወቂያ አድራሻ ሳይገደብ በየአቅራቢያው እንዲሰጥ ተፈቀደ April 2, 2025 በመዲናዋ የተለያዩ ህገ-ወጥ ነጋዴዎች ላይ አስተዳደራዊ እና ህጋዊ እርምጃ ተወሰደ March 8, 2025 አዲስ አበባን ያስዋቡ የልማት ፕሮጀክቶች ትውልድ ተሻጋሪ አሻራዎች ናቸው- የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች December 27, 2024