በመዲናዋ የምርት ጥራትና ህገ ወጥ ግብይትን መቆጣጠር የሚያስችሉ አሰራሮች ተዘርግተዋል-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ

AMN – ታኅሣሥ 8/2017 ዓ.ም

በአዲስ አበባ ከተማ የምርት ጥራትና ህገ ወጥ ግብይትን መቆጣጠር የሚያስችሉ የተለያዩ አሰራሮች መዘርጋታቸውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ ገለጸ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ ምክትል ኃላፊ ፍሰሃ ጥበቡ በንግድ እንቅስቃሴው ህጋዊ ነጋዴዎችን የማበረታታትና ህገ ወጥነትን የመከላከልና የመቆጣጠር ስራ ተጠናክሮ ቀጥሏል ብለዋል።

በተለይም ያለ ደረሰኝ የሚደረግ ግብይትንና የምርት ጥራት መጓደልን ለመቆጣጠር እንዲሁም የአሰራር ግድፈቶችን ለማስተካከል የተጠናከረ ክትትልና ቁጥጥር እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል።

በመዲናዋ የንግድ ስርዓቱ በውድድር ላይ የተመሰረተ፣ ፍትሃዊና ጤናማ እንዲሆን ከማድረግ ባለፈ የምርት ጥራትና ህገ-ወጥ ግብይትን መቆጣጠር የሚያስችሉ የተለያዩ ተግባራት እየተከናወኑ ይገኛል ብለዋል፡፡

ለዚህም የተቋሙን አገልግሎት አሰጣጥ ዲጂታላይዝ በማድረግ ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት በመስጠት የክትትል ቁጥጥርና ድጋፍ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን መግለጻቸውን ኢዜአ ነው የዘገበው፡፡

ለንግዱ ማህበረሰብ አጠቃላይ መረጃ በቀላሉ ተደራሽ የሚሆንበት የመረጃ ቋት አሰራር መዘርጋቱንም አስታውቀዋል፡፡

በከተማ አስተዳደሩ ኢኮኖሚ ዘርፍ የሚመራ ግብረ ሃይል ተቋቁሞ የክትትል ቁጥጥርና ድጋፍ ስራዎች በትኩረት እየተከናወኑ መሆኑንም ጨምረው ተናግረዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review