AMN-ጥቅምት 26/2017 ዓ.ም
በመጀመሪያዉ ሩብ ዓመት ከባለድርሻ አካላት ጋር በተከናወነ የቅንጅት ስራ የደንብ መተላለፍ ምጣኔን በ61 በመቶ መቀነስ መቻሉን የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን
ባለስልጣኑ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የሰላም፣ፍትህና መልካም አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በተገኘበት በሩብ ዓመቱ ከባለድርሻ አካላት ጋር የተከናወኑ ስራዎችን ገምግሟል።
በግምገማው ላይ የቀረበው ሪፖርት እንዳመለከተው በሩብ ዓመቱ የመሬትና ህገወጥ ንግድን ከመከላከል አንፃር ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን አበረታች ስራዎች ተሰርተዋል።
በሩብ ዓመቱ በኮሪደር ልማትና በመልሶ ማልማት ምክንያት ክፍት የሆኑ 6 ሺህ 459 ቁራሽ መሬቶች እንዲጠበቁ ማድረጉን ባለስልጣኑ ጠቅሷል።
የደንብ መተላለፍና ተያያዥ ህገወጥ ተግባራትን የመከላከልና የመቆጣጠር ስልጣን የተሰጠው ተቋሙ ከመቅጣት ይልቅ ለግንዛቤና ለማስተማር ስራዎች ትኩረት እንደሚሰጥ አመልክቷል።
በዚህም ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ እየተፈጠረ ያለ የደንብ መተላለፍ ምጣኔን መቀነስ መቻሉንም ነው ባለስልጣኑ የገለጸው።
በትዕግስት መንግስቱ