AMN – የካቲት 17/2017 ዓ.ም
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ወልቂጤ ከተማ ህዝባዊ ኮንፈረንስ መካሄድ ጀምሯል፡፡
በመድረኩ ላይ የከተማ እና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ወይዘሮ ጫልቱ ሳኒ÷ የቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ጌታሁን አብድሳ እና ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል፡፡
በህዝባዊ ኮንፈረንሱ “ከቃል እስከ ባህል” በሚል መሪ ሃሳብ የብልፅግና ፓርቲ 2ኛ መደበኛ ጉባዔ ላይ በተላለፉ ውሳኔዎችና አቅጣጫዎች ዙሪያ ምክክር እየተደረገ ይገኛል።

በኮንፈረንሱ ከህብረተሰብ ለሚነሱ ጥያቄዎች የብልፅግና ፓርቲ ስራ አስፈጻሚና የፓርቲው ምክር ቤት አባላት ምላሽና ማብራሪያ እንደሚሰጡ ተመላክቷል፡፡
በተመስገን ይመር