
AMN ህዳር 17/2017 ዓ .ም
በማዕከላዊ ጎንደር ዞን አምባ ጊዮርጊስ፣ ገደብየና ወርቀ ደሙ አካባቢዎች ለዓመታት የህብረተሰቡን ሰላም ሲያውኩና ሲዘርፉ የነበሩ የፅንፈኛው ቡድን አባላት ለሰሜን ምዕራብ ዕዝ ክፍለ ጦር እጅ ሰጥተዋል።
በቀጠናው የሚገኘው ክፍለ ጦር አዛዥ ኮሎኔል ተክሌ አጋ በቀጠናው በተደጋጋሚ ሰላማዊ ውይይት በማድረግ ከጦርነት ይልቅ ሰላምን አማራጭ አድርገውና በፍቃደኝነት ሃያ አምስት ታጣቂዎች ከ16 ክላሽ፣ 01 አርባ ጎራሽ እና ሌላም በመያዝ እጃቸውን መስጠታቸውን ገልፀዋል።

የአካባቢው ህብረተሰብ መከላከያ ሠራዊቱ በሚያደርጋቸው ስምሪቶችና በሚወጣቸው ግዳጆች እያሳየ ያለው ድጋፍና እገዛ የሚደነቅ በመሆኑ ለቀጣይም አጠናክረው መቀጠል ይገባቸዋል ሲሉ የክፍለ ጦር አዛዥ መናገራቸውን የሀገር መከላከያ ሰራዊት በማህበራዊ ትስስር ገፁ አመልክቷል።
ትክክለኛውን የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዲጂታል ሚዲያ የትስስር አውታሮችን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑን!