AMN- ጥቅምት 30/2017 ዓ.ም
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 አዲሱ ገበያ አካባቢ ከሚገኙ የቅዳሜና እሁድ ገበያዎች ሸማቾች ካለፉት ሳምንታት በተሻለ ደረጃ የሽንኩርትና የቲማቲም እንዲሁም የድንች ዋጋ ቅናሽ አሳይቷል ብለዋል፡፡
በገበያዎቹም ሽንኩርት በኪሎ 50 ብር፣ ቲማቲም በኪሎ 25 ብር ፣ ቀይ ስር በኪሎ 30 ብር፣ ድንች በኪሎ 20 ብር ለመሸመት ችለናል ሲሉም ሸማቾች መናገራቸውን ቢሮው ገልጿል፡፡
ሸማቾቹ በአሁኑ ወቅት የአትክልትና ፍራፍሬ ምርቶች ቅናሽ እያሳዩ በመምጣታቸው እንደ ጤፍ፣ ስንዴና መሰል የእህል ምርቶች ላይም ተገቢው የዋጋ ቁጥጥር በማድረግ ለውጥ ማምጣት ይገባልም ብለዋል፡፡
አክለውም የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ በመንግስት የገበያ ማዕከላት የሚቀርቡ ምርቶችን ዋጋ ለነዋሪው ማሳወቅ መጀመሩ መልካም ሲሆን ማዕከላቱን ማስተዋወቅ እና የዋጋ ቁጥጥሩን ማጠናከር እንደሚገባውም ማንሳታቸውን ከቢሮው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡