AMN-የካቲት 15/2017 ዓ.ም
“ከቃል እስከ ባሕል” በሚል መሪ መልዕክት ሕዝባዊ ኮንፈረንስ በባሕርዳር ከተማ እየተካሄደ ነው።
ሕዝባዊ ኮንፈረንሱ የብልጽግና ፓርቲ በሁለተኛው መደበኛ ጉባኤ ባሳለፋቸው ውሳኔዎች እና ባስቀመጣቸው አቅጣጫዎች ላይ ያተኮረ መሆኑን ከአማራ ክልል ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
በመድረኩ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መሥተዳደር ጥላሁን ከበደ፣ የብልጽግና ፓርቲ የሕዝብ እና የዓለም አቀፍ ግንኙነት ዘርፍ ኀላፊ ቢቂላ ሁሪሳ (ዶ.ር)፣ የባሕርዳር ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ጎሹ እንዳላማው ጨምሮ ሌሎች የመንግሥት እና የፓርቲው ከፍተኛ የሥራ ኀለፊዎች ተገኝተዋል።