AMN – የካቲት 13/2017 ዓ.ም
በብልፅግና ፓርቲ 2ኛ መደበኛ ጉባኤ የተቀመጡ አቅጣጫዎች በተግባር የታጀቡ እንዲሆኑ በትኩረት እንደሚሰራ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ የፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰዉ ሀብት ልማት ቢሮ ሀላፊ ጀማሉ ጀንበር (ዶ/ር) ተናገሩ፡፡
በብልፅግና ፓርቲ 2ኛ መደበኛ ጉባኤ በተቀመጡ አቅጣጫዎች ዙሪያ በጉለሌ ክፍለ ከተማ ህዝባዊ ዉይይት እየተካሄደ ነዉ፡፡
በውይይት መድረኩ ላይ የተገኙት በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ የፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰዉ ሀብት ልማት ቢሮ ሀላፊ ዶክተር ጀማሉ የብልፅግና ፓርቲ በ2ኛ መደበኛ ጉባኤዉ ያስቀመጣቸዉን አቅጣጫዎች ለመተግበር በትጋት ይሰራል ብለዋል፡፡
በመድረኩ ላይ የመዲናዋ ከፍተኛ አመራሮች እና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል፡፡
በተመስገን ይመር