የካቲት 13/2017 ዓ.ም
“የሚለውጥ ቃል የሚፀና ባህል ለኢትዮጵያ ልዕልና” በሚል መሪ ሀሳብ በሚካሄደው ህዝባዊ ውይይት ላይ የክፍለ ከተማው ነዋሪዎች ፣ የፓርቲ እና የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
ከጥር 23 እስከ 25 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ 2ኛ መደበኛ ጉባኤውን ያካሄደው ብልጽግና ፓርቲ 10 ዋና ዋና የትኩረት አቅጣጫዎችን ማስቀመጡ ይታወሳል።
ብሔራዊ ገዥ ትርክት መገንባት ፣ ዘላቂ ሰላምን ማስፈን ፣ ዜጎች የሚተማመኑበት የፍትህ ስርዓት መዘርጋት ፣ ኢኮኖሚያዊ አቅምን ማሳደግ ፣ የሀገርን ብሔራዊ ጥቅም ማስከበር እና ጠንካራ ተቋም መገንባት ከፓርቲው የጉባኤ አቅጣጫዎች ውስጥ ቀዳሚዎቹ ናቸው።
የፓርቲው አቅጣጫዎች ሀገርን የሚያሻግሩ፣ አዲስ አበባንም ከስምና ክብሯ ጋር የሚያዋህዱ ውሳኔዎች በመሆናቸው ለተግባራዊነታቸው ሁሉም በጋራ ሊሰራ እንደሚገባም በውይይቱ ላይ ተነስቷል።
ብልፅግና ፓርቲ በሀገር አቀፍ ደረጃ 15 ነጥብ 7 ሚሊዮን አባላት እንዳሉት ማስታወቁ አይዘነጋም።
በካሳሁን አንዱዓለም