በታሪካዊቷ የጅማ ከተማ ለ6ኛ ጊዜ የሚካሄደውን ሀገር አቀፍ የመላው ኢትዮጵያ ጨዋታዎችን ማስጀመራቸውን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ ገለፁ

You are currently viewing በታሪካዊቷ የጅማ ከተማ ለ6ኛ ጊዜ የሚካሄደውን ሀገር አቀፍ የመላው ኢትዮጵያ ጨዋታዎችን ማስጀመራቸውን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ ገለፁ

AMN- ሰኔ 10/2017

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ ለዘመናት የኅብረ ብሔራዊነት መናኸሪያ በሆነችው በአባ ጅፋር ሀገር፣ በንግድ፣ በባህል፣ በሃይማኖትና በትምህርት ኢትዮጵያውያን ከአራቱም ማዕዘን ሲገናኙባት የኖረች ከተማ ጅማ ገብተናል ሲሉ በይፋዊ ማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ ገልጸዋል፡፡

በታሪካዊቷ ከተማችን ለስድስተኛ ጊዜ የሚካሄደውን ሀገር አቀፍ የመላው ኢትዮጵያ ጨዋታዎችን እናስጀምራለንም ብለዋል።

ጅማ ከተማ ስንደርስ ደማቅ አቀባበል ላደረጉልን የፌደራል አመራሮች፣ የኦሮሚያ ክልል አመራሮች እና የጅማና አካባቢው ነዋሪዎች ሁሉ የከበረ ምስጋናም አቅርበዋል ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review