
AMN – ታኅሣሥ 30/2017 ዓ.ም
ባለፉት የለውጥ ዓመታት በቴክኒክና ሙያ ተቋማት በተከናወኑ የለውጥ ስራዎች አዳዲስ ሀብቶች መፍጠር መቻሉን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ገለጹ።
የስልጠና ተቋማቱ ዜጎች ሀብት የሚፈጥር የሥራ ሃሳብ አመንጪ እና ችግር ፈቺ ቴክኖሎጂ አፍላቂ እንዲሆኑ እያገዙ መሆኑን ተናግረዋል።
ሚኒስትሯ እንዳሉት የክህሎት ልማት በማጎልበት ለኢኮኖሚ ዕድገት ዘላቂነትና ስራ አጥነት ቅነሳ አስፈላጊ እንደሆኑ ገልጸዋል።
ለክህሎት ልማት ደግሞ የስልጠና ተቋማትን የማመዘን፣ መሠረተ ልማት ማሟላትና ሌሎች ዘርፈ ብዙ ስራዎች ማከናወን ይጠይቃል ብለዋል።
ባለፉት የለውጥ ዓመታት በቴክኒክና ሙያ ተቋማት በተከናወኑ የለውጥ ስራዎች አዳዲስ ሀብቶች መፍጠር መቻሉን ጠቁመዋል።
ተቋማቱ የሚያወጧቸውን ተማሪዎች ሀብት ፈጣሪ የሥራ ሃሳብ አመንጪና ችግር ፈቺ ቴክኖሎጂ አፍላቂ እንዲሆኑ እያገዙ ነው ብለዋል።
በቀጣይ የቴክኒክና የሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት በዚህ ቅኝት እንዲሰሩና ተደራሽነታቸው እንዲሰፋ እንደሚሰራ አረጋግጠዋል።
ይህም ኢትዮጵያ ውስጥ ዝንባሌና መክሊት ያላቸው ዜጎች በማዕከላቱ ስራ መፍጠር እንዲችሉ እንደሚያደርግ መግለፃቸውን ኢዜአ ዘግቧል።