AMN – የካቲት 16/2017 ዓ.ም
በቴክኖሎጂ የታገዘ የቁጥጥር ስራ ተግባራዊ በማድረግ የደንብ መተላለፎችን መቀነስ መቻሉን የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ ገለጹ፡፡
የአራዳ ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት የ2017 ዓ.ም በጀት ዓመት የመጀመሪያ 6 ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ፣ የእውቅናና ሽልማት እንዲሁም የተሀድሶ ፕሮግራም አካሄዷል።

የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ በበጀት ዓመቱ 6 ወራት ሰፋፊ ስራዎች በመስራት የደንብ መተላለፍ መቀነስ መቻሉን ተናግረዋል፡፡
ባለስልጣን መስርያ ቤቱ ራሱን የአዳዲስ ቴክኖሎጂ ባለቤት በማድረጉ የደንብ መተላለፎች እንዲቀንስ ተችሏል ብለዋል።

የአራዳ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ጌታሁን አበራ፣ የደንብ ማስከበር ባለስልጣን በርካታ ስራዎችን መስራት መቻሉንና በአደባባይ የሚከበሩ በዓላት ስኬታማ ሆነው እንዲጠናቀቁ የተሰራው ስራ የሚያስመሰግን መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በመሀመድኑር አሊ