በትግራይ ክልል ለሚካሂደው ምክክር የሁሉም ባለድርሻ አካይ ድጋፍ ያስፈልጋል- ኮሚሽኑ

You are currently viewing በትግራይ ክልል ለሚካሂደው ምክክር የሁሉም ባለድርሻ አካይ ድጋፍ ያስፈልጋል- ኮሚሽኑ

AMN – ሚያዚያ 4/2017 ዓ.ም

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከትግራይ ክልል ሲቪክ ማህበራት አመራሮች ጋር ተወያይቷል፡፡

በውይይቱ ላይ ንግግር ያደረጉት ዋና ኮሚሽነር መሥፍን አርአያ (ፕሮፌሰር) “በትግራይ ክልል ከግጭቶች ማግስት የተፈጠረውን ማህበራዊ ችግር ለመፍታት ብዙ መወያየትና መነጋገር ያስፈልጋል” ብለዋል፡፡

ኮሚሽኑ በክልሉ ያለውን ነባራዊ ሁኔታ እንደሚገነዘብ የገለፁት ዋና ኮሚሽነሩ፤ ከዚህ ቀደም በክልል ከሚገኙ ባለድርሻ አካላት ጋር የተለያዩ ውይይቶች ሲያከናውን መቆየቱን ገልጸዋል፡፡

ኮሚሽነር አምባዬ ኦጋቶ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ ሲቪክ ማህበራት የማህበረሰቡን ድምፅ በምክክር መድረኮች ከማንፀባረቅ ባሻገር ሂደቱ አካታች እንዲሆን ለማድረግ የማይተካ ሚና እንዳላቸው ተናግረዋል፡፡

“ኮሚሽኑ ገለልተኛ ነው ወይስ አይደለም” የሚለውን ቀርቦ በተግባር መፈተሸ እንደሚያስፈልግ የገለፁት ኮሚሽነር አምባዬ (ዶ/ር) ፤ “በትግራይ ክልል የሚኖረው ሂደት የተለየ ስልት እንደሚስፈልገው ከዛሬው ውይይት ተገንዝበናል” ብለዋል፡፡

በቀጣይ በትግራይ ክልል ከማህበረሰቡ፣ ከመንግስት ኃላፊዎችና ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይቶች እንደሚደረጉ መገለጹን ከኮሚሽኑ ያገኘነዉ መረጃ ያመላክታል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review