በቻይና የሚገኙ ኩባንያዎችና ኢንቨስተሮች በኢትዮጵያ በጤናው ዘርፍ ለመስራት ፍላጎት እንዳላቸው ገለጹ

You are currently viewing በቻይና የሚገኙ ኩባንያዎችና ኢንቨስተሮች በኢትዮጵያ በጤናው ዘርፍ ለመስራት ፍላጎት እንዳላቸው ገለጹ

AMN-የካቲት 18/2017 ዓ.ም

በሺንዢን ቻንዩአን ኔትወርክ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ካምፓኒ ዋና ስራ አስፈጻሚ ሞ ቺን የተመራ የኢንቨስተሮች ልኡካን ቡድን ከጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ ጋር ተወያይቷል፡፡

ውይይቱ የጤና ዘርፍ ዲጂታላይዜሽን፣ ስማርት የህክምና መሳሪያዎች፣ እና የመድሃኒት አቅርቦት ላይ ያተኮረ መሆኑ ተገልጿል።

የኢትዮጵያ መንግስት በሁሉም ዘርፍ ሪፎርም እያደረገ መሆኑን ያስታወሱት የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ፣ የጤናው ዘርፍ ዲጂታላይዜሽን ላይ በትብብር ለመስራት ከምንግዜውም በላይ አመቺ መሆኑን አስረድተዋል።

ቻይና ከኢትዮጵያ ጋር በትብብር የመስራት የረጅም ጊዜ ልምድ አላት ያሉት የሺንዢን ቻንዩአን ኔትወርክ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ካምፓኒ ዋና ስራ አስፈጻሚ ሞ ቺን፤ በተለይም የጤና ዲጂታይዜሽን፣ ስማርት ሜዲካል መሳሪያዎች ፣ እና የመድሃኒት ቅርቦት ላይ ከጤና ሚኒስቴር ጋር በትብብር ለመስራት ያላቸውን ፍላጎት አሳይተዋል።

ይህ ትብብር የኢትዮጵያን የጤና ዘርፍ አገልግሎት ለማሻሻል እና የዲጂታል ቴክኖሎጂን በመጠቀም የጤና አገልግሎቶችን ለህብረተሰቡ በተመቻቸ ሁኔታ ለማቅረብ ያለመ መሆኑን አክለዋል።

በተጨማሪም ኢትዮጵያውያን ሃኪሞችን በተመረጡ ከፍተኛ የህክምና ስልጠና ዘርፎች ላይ ስልጠና መስጠት በሚቻልበት መንገድ ዙሪያ ውይይት ተደርጓል። ይህ እንቅስቃሴ የኢትዮጵያን የጤና ባለሙያዎች አቅም ለማሳደግ እና የቻይናን የጤና ቴክኖሎጂ እና የሕክምና ዘርፍ እውቀት ለማጋራት ያለመ መሆኑን የጤና ሚኒስቴር መረጃ ያሳያል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review