
የበዓል ስራዎቸን በሚከናወኑበት ጊዜ ሁሉንም ስራዎች በተመሳሳይ ጊዜ ከማከናወን መቆጠብና ስራዎችን በቅድመ ተከተል እንዲሁም እንደቤተሰብ አባል ብዛትና ችሎታ ስራን መከፋፈል ያስፈልጋል።
በአንድ ኤሌክትሪክ ማከፋፈያ ላይ ሶኬቶችን ደራርቦ አለመጠቀም ፣ ጋዝ ሲሊንደር ከመለኮስዎ በፊት በጋስ ሲሊንደር መስመር ዉስጥ ያፈተለከ ጋዝ አለመኖሩን ማረጋገጥ ።
ከሰል በመጠቀም የከሰል ምድጃዉን ከቤት ዉጪ በማድረግ ከሰሉ ጢሱን እንዲጨርስ ማድረግና ወደቤት ካስገባን በኋላም በርና መስኮት በመክፈት በቂ የአየር ምልልስ እንዲኖር በማድረግና ስራችንን ካጠናቀቅንም በኋላ ምድጃዉን ከቤት በማዉጣትና እሳቱን በዉሀ በማጥፋት ቤቱን ማናፈስ ።
ለክብረ በዓሉ ወይም ለብርሀን አገልግሎት የምንለኮሰዉ ሻማ ከመጋረጃና ከሶፋ እንዲሁም ከሌሎች ተቀጣጣይ ነገሮች ጋር እንዳይገናኝ ጥንቃቄ ማድረግና ከመተኛታችን በፊት ወይም ከቤት በምንወጣ ጊዜ የተለኮሰዉን ሻማ ማጥፋታችንን ማረጋገጥ ያስፈልጋል።
በንግድ ማዕከላትም ነጋዴዎች የንግድ ሱቆቻቸዉን ዘግተዉ ከመዉጣታቸዉ በፊት የተዘነጉ የኤሌክትሪክ ሶኬቶችን እና የተለኮሱ ሻማዎች ካሉ መጥፋታቸዉንና መቋረጣቸዉን ማረጋገጥ።
የጥንቃቄ ተግባራትን በመፈጸም በዓሉ ያለአደጋ ክስተት በሰላም እንዲያልፍ አደጋን አስቀድሞ በመከላከል ህብረተሰቡ ኃላፊነቱን እንዲወጣ የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አሳስቧል፡፡
ከዚህ ዓልፎ ለሚያጋጥሙ ማንኛውም አደጋዎች ኮሚሽን መ/ቤቱ አስፈላጊዉን ቅድመ ዝግጅት ማድረጉን የገለጸ ሲሆን ለእሳትና ለሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች እንዲሁ ለአንቡላንስ አገልግሎቶች በ939 ፈጥነዉ እንዲያሳውቁ ሲል ጥሪ አቅርቧል፡፡
All reactions:
5858