AMN-የካቲት 27/2017 ዓ.ም
የአዲስ አበባ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ከአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጋር “የእምነት ተቌማት በሰላም ግንባታ እና በልማት ሂደት ዉስጥ ያላቸው ሚና “በሚል መሪ ሃሣብ የማጠቃለያ መድረክ በአድዋ ድል መታሰቢያ እየተካሄደ ነዉ::
የሃይማኖት ተቋማት ከዚህ ቀደም ለሠላም እና ልማት በሰሯቸው ስራዎች በርካታ ውጤቶች መመዝገባቸው በመድረኩ ላይ ተገልጿል::
ከነዚህ መካከል ህዝባዊ እና ሃይማኖታዊ በዓላት እሴታቸውን ጠብቀውና በሠላም እንዲከበሩ ማስቻል ተጠቃሽ ነው፡፡
በከተማዋ እየተከናወነ ያለዉ የኮሪደር ልማት እና የወንዝ ዳርቻ ልማት ስራዎች በተያዘላቸው የጊዜ ገደብ እንዲከናወኑ የሃይማኖት ተቌማት ሚና ከፍተኛ እንደነበረም ተመላክቷል::
እነዚህ ዘርፈ ብዙ ተግባራት እና ስኬቶች የሃይማኖት አባቶች ከመንግስት ጋር ተቀራርበው በመስራት ያመጧቸው ውጤቶች በመሆናቸው ተቋማቱ ይበልጥ ተቀራርበው እና በአንድነት ተጠናክረው ሊያስቀጥሉ ይገባል ነዉ የተባለው።
በመድረኩ የሃይማኖት አባቶች፣ አባ ገዳዎች ሀደ ሲንቄዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተሳትፈዋል::
በአንዋር አሕመድ