AMN – ታኅሣሥ 17/2017 ዓ.ም
በአዲስ አበባ እየተካሄደ የሚገኘው የኮሪደር ልማት እና አጠቃላይ የከተማ ልማት ስራ ከተማዋን ከማዘመንና ለኑሮ ምቹ ከማድረግ ባለፈ የነዋሪውን ህይወት በተጨባጭ የሚያሻሽል ሰው ተኮር መሆኑን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ ተናገሩ፡፡
የብልጽግና ፓርቲ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት በአዲስ አበባ ከተማ የተገነቡ የኮሪደር ልማት እና ሌሎች የከተማ ልማት ስራዎችን ጎብኝተዋል፡፡
ላለፉት ሁለት ቀናት በተለያዩ ሀገራዊ ጉዳዮች እና የፓርቲ አጀንዳዎች ላይ ሲመክሩ የቆዩት የብልጽግና ፓርቲ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት በአዲስ አበባ ከተማ የተገነቡ የኮሪደር ልማት እና ሌሎች የከተማ ልማት ስራዎችን ጎብኝተዋል፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ የሚገነቡ የልማት ስራዎች ትላልቅ ከተሞች ሲገነቡ እንዲሟሉ የሚጠበቁ መሰረተ ልማቶች መሆናቸውን ተመልክተናል ብለዋል በጉብኝቱ ላይ የተገኙት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ የልማት ስራ ከተማዋን ከማዘመንና ለኑሮ ምቹ ከማድረግ ባለፈ የነዋሪውን ህይወት በተጨባጭ የሚያሻሽል ሰው ተኮር መሆኑንም ነው ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የገለጹት፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ የሚሰራው ስራ ለአፍሪካ ከተሞች ጭምር አርያ የሚሆን እና አዲስ አበባ ከተማን በሌላ አዲስ ምዕራፍ ላይ የሚያስቀምጡ እና የተቀናጁ ናቸው ያሉት ደግሞ የገንዘብ ሚኒስትር ሩ አቶ አህመድ ሽዴ እና የስራ እና ክህሎት ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፈርያት ካሚል ናቸው፡፡
የከተማዋ የልማት ስራ ስኬት ለሌሎች ከተሞች አርዓያ የሚሆን እና በተሞክሮነት የሚወሰድ መሆኑንም ነው ሚኒስትሮቹ የገለጹት፡፡
በሁለተኛ ምዕራፍ የኮሪደር ልማት የተካተቱት የእንጦጦ ወዳጅነት አደባባይ ፒኮክ ፓርክ የወንዝ ዳርቻ ልማት፣የካዛንችስ አካባቢ የኮሪደር ልማት እና መልሶ ማልማት፣ የፒያሳ አካባቢ የመልሶ ማልማት እና ልዩ ልዩ መሰረተ ልማት ግንባታዎች፣ የመንገድእና የአረንጓዴ ልማት ስራዎች ፣ የገላን ጉራ እና የቃሊቲ የልማት ተነሺዎች መኖሪያ መንደሮች እና መሰረተ ልማቶች፣ የነገዋ የሴቶች ተሃድሶ እና ክህሎት መባልጸጊያ ማዕከል እና ብርሃን የአይነስውራን አዳሪ ትምህርት ቤት ከተጎበኙት መሰረተ ልማቶች መካከል ተጠቃሽ ናቸው፡፡
በሰብስቤ ባዩ