በአዲስ አበባ ከ835 ሺ በላይ ተማሪዎች በቀን ሁለት ጊዜ የምገባ አገልግሎት ያገኛሉ- ከንቲባ አዳነች አቤቤ

You are currently viewing በአዲስ አበባ ከ835 ሺ በላይ ተማሪዎች በቀን ሁለት ጊዜ የምገባ አገልግሎት ያገኛሉ- ከንቲባ አዳነች አቤቤ

AMN-የካቲት 12/2017 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት የ2017 ዓ.ም 4ኛ የስራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ጉባኤውን እያካሄደ ይገኛል፡፡

በምክር ቤቱ ተገኝተው የከተማ አስተዳሩን የ6 ወራት የሥራ ክንውን እያቀረቡ የሚገኙት ከንቲባ አዳነች አቤቤ በተለይም በትምህርት ዘርፍ ፍትሃዊ ሽፋንና ተደራሽነትን ከማሳደግ አንፃር አበረታች አፈፃፀም መመዝገቡን ገልፀዋል፡፡

በአሁኑ ሰዓት የተማሪ ቅበላን ከ1 ነጥብ 2 ሚሊዮን በላይ ማድረስ የተቻለ ሲሆን ይህም አፈፃፀሙን 106 በመቶ አድርጎታል፡፡ አፈፃፀሙም ከባለፈው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር ከ98ሺ በላይ ብልጫ እንዳለው ተናግረዋል፡፡

የትምህርት ፍትሀዊነትን ከማስፈን አንፃር በሁሉም ትምህርት ቤቶች የልዩ ፍላጎት ትምህርትን በማስፋፋት የተማሪዎች ቁጥር 33ሺ 672 ደርሷል፡፡ አፈፃፀሙንም መቶ በመቶ ማድረስ ተችሏል ነው ያሉት።

ባለፉት 6 ወራት በትምህርት ለትውልድ ንቅናቄ በገንዘብ፣ በዓይነት፣ በጉልበት እና በእውቀት በድምሩ ከ4 ቢሊዮን ብር በላይ በመሰብሰብ የትምህርት ግብዓትን የማሟላት ስራ ተሰርቷል።

የተማሪ የቅበላ አቅም ለማሻሻልና የትምህርት ፍትሀዊነት ለማረጋጋጥ የተሰራው ስራ አበረታች ነው ብለዋል።

የተማሪዎችን የትምህርት ተሳትፎ በዘላቂነት ከማሳደግ እና ግብዓትን ከማቅረብ አንጻርም መቶ በመቶ መከናወኑን አንስተዋል፡፡

በተማሪ ምገባ አገልግሎትም 835 ሺ 69 ተማሪዎችን በቀን ሁለት ጊዜ መመገብ ተጠናክሮ መቀጠሉን ያስታወቁት ከንቲባ አዳነች በተሠራው አበረታች ተግባርም አፈፃፀሙ ከመቶ ደርሷል ብለዋል፡፡

የትምህርትና ስልጠና ጥራት ተገቢነትን ለማረጋገጥ በተሰራው ስራም በ126 ተቋማት ላይ የውጭ ኢንስፔክሽን በማካሄድ የደረጃ ምደባ እና የኢንስፔክሽን ሥራ ተደራሽ ተደርጓል።

ለትምህርትና ስልጠና የእውቅና እና የእድሳት አገልግሎት ጥያቄ ላቀረቡ 660 ተቋማትም የእውቅና እና የእድሳት አገልግሎት ተሰጥቷል ብለዋል።

በማሬ ቃጦ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review