በአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ማሾ ኦላኖ የተመራ ቡድን የአዲስ አበባ ፖሊስ የደረሰበትን ደረጃ እየጎበኘ ነው

You are currently viewing በአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ማሾ ኦላኖ የተመራ ቡድን የአዲስ አበባ ፖሊስ የደረሰበትን ደረጃ እየጎበኘ ነው

AMN – የካቲት 25/2017 ዓ.ም

በአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ማሾ ኦላኖ የተመራ ቡድን የአዲስ አበባ ፖሊስ የደረሰበትን ደረጃ እየጎበኘ ነው፡፡

በጉብኝት መርሃ ግብሩ አቶ ማሾን ጨምሮ የአዲስ አበባ ምክር ቤት የህግ እና ፍትህ አስተዳደሮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ሙሉነህ ደሳለኝ፣የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽነር ጌቱ አርጋው እና ሌሎች የምክር ቤት አባላት እና የአዲስ አበባ ፓሊስ አመራሮች እየተሳተፉ ነው።

በዚሁ ወቅት መልዕክት ያስተላለፉት የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጌቱ አርጋው፣ተቋሙ የህዝብ ጥያቄዎችን መሰረት ያደረጉ በርካታ ሪፎርሞች መካሄዳቸውን ገልጸዋል።

በተጨማሪም በቴክኖሎጂ አደረጃጀት እና የሰው ሃይል ራሱን በሚገባ ገንብቷልም ብለዋል።

ባለፉት ዓመታት በዘርፉ በተከናወኑ ስራዎች በርካታ ሀይማኖታዊ፣ባህላዊ እና ህዝባዊ በላት በድምቀት እንዲከበሩ መሆናቸውንም አብራርተዋል።

በዚህ ሂደት የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ እና የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት የላቀ አበርክቶ ነበራቸውም ብለዋል።

በሀብታሙ ሙለታ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review