AMN – መጋቢት 11/2017 ዓ.ም
የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በመዲናዋ ከሚገኙ አቅመ ደካሞች እና ዝቅተኛ ገቢ ካላቸዉ የእስልምና እምነት ተከታዮች ጋር የኢፍጣር መርሃ ግብር አከናውነዋል።
ከንቲባዋ መርሐግብሩን አስመልክተው በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባጋሩት መልዕክት፤ይህን የጾም እና የጸሎት ወቅት የእምነቱ አስተምሮ በሚያዘው መሰረት ድሆችን እና ጠያቂ የሌላቸዉን ወገኖች መርዳት፣ መደገፍ እና አቅመ ደካሞችንም በማሰብ መሆን አለበት ብለዋል።

‹እኛም ፆሙን ምክንያት በማድረግ በከተማችን በሚገኙ 24ቱ የተስፋ ብርሃን የምገባ ማዕከላት ዘወትር ማታ ማታ ለአቅመ ደካማ እና ለተለያዩ ማህበራዊ ችግሮች ለተጋለጡ ሰዎች የአፍጥር መርሃ ግብር በማዘጋጀት ነዋሪዎቻችንን እያስፈጠርን እንገኛለን› ሲሉም አስፍረዋል::
ከንቲባዋ ለ1446 የታላቁ የረመዳን የፆም ወር እንኳን አደረሳችሁም ብለዋል::