በአዲስ አበባ ከተማ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎች የከተማዋን ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነት የሚያሳድጉ ናቸው

You are currently viewing በአዲስ አበባ ከተማ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎች የከተማዋን ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነት የሚያሳድጉ ናቸው

AMN – ሚያዝያ 14/2017 ዓ.ም

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ተጠሪ ተቋማት እና የብልፅግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት የሥራ ኃላፊዎችና ሰራተኞች በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ የተለያዩ የልማት ስራዎችን እየጎበኙ ነው።

ጉብኝቱ በከተማዋ የተከናወኑ እና በመከናወን ላይ የሚገኙ የኮሪደር ልማት ስራዎችን፣ የመልሶ ማልማትና የወንዝ ዳርቻ ፕሮጀክቶችን ጨምሮ ሌሎች በርካታ የልማት ሥራዎችን ያካተተ መሆኑ ተጠቁሟል።

በአዲስ አበባ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎች ለነዋሪዎች ምቹ አካባቢ የሚፈጥሩና የከተማዋን ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነት በእጅጉ የሚያሳድጉ መሆናቸው መገለጹን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

የልማት ሥራዎቹ አዲስ አበባን የተቀናጀ የመሠረተ ልማት የተሟላላት ከተማ እንድትሆን የሚያስችሉ መሆናቸውም ተመላክቷል፡፡

በከተማዋ ባለፉት ጥቂት ዓመታት የዓድዋ ድል መታሰቢያ፣ የአዲስ ዓለም ዓቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል፣ የነገዋ የሴቶች ተሐድሶ ማዕከል፣ የተለያዩ ሰው ተኮር ፕሮጀክቶች እንዲሁም ሌሎች በርካታ የልማት ስራዎች መከናወናቸው ይታወቃል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review