በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ አምራቾችና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት የወንዞችን ደህንነት እንዲጠብቁ ጥሪ ቀረበ

You are currently viewing በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ አምራቾችና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት የወንዞችን ደህንነት እንዲጠብቁ ጥሪ ቀረበ

AMN – መጋቢት 2/2017 ዓ.ም

በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ አምራቾችና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት የወንዞች ዳርቻ ልማትና ብክለት ለመከላከል የወጣውን ደንብ ቁጥር 180/2017 ተግባራዊ በማድረግ የወንዞችን ደህንነት እንዲጠብቁ የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ጥሪ አቀረበ::

ባለስልጣኑ የወንዞች ዳርቻ ልማትና ብክለት ለመከላከል የወጣውን ደንብ ቁጥር 180/2017 በተመለከተ ለአምራቾችና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ እያካሄደ ነዉ::

በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ ወንዞች በርካታ ቢሆኑም በከፍተኛ ሁኔታ ለብክለት ተደርገዋል። ለዚህ ደግሞ ግለሰቦችና ድርጅቶች ወደ ወንዞቹ በሚለቋቸው ንፁህ ያልሆኑ ፍሳሽ እና ተያያዥ ቆሻሻዎች እንደሆነ ጥናቶች ያመለክታሉ።

ይህንን ለመከላከልና የወንዞችን ደህንነት ለመጠበቅ በአስተዳደሩ እየተከናወነ ካለዉ የወንዞች ልማት ጐን ለጐን አዲስ ደንብና መመሪያ አዘጋጅቷል::

በከተማ የሚገኙ አምራቾችና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት የወንዞች ዳርቻ ልማትና ብክለት ለመከላከል የወጣውን ደንብ ተግባራዊ በማድረግ፣ የወንዞችን ደህንነት እንዲጠብቁና ከተጠያቂነት እንዲድኑ የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን አሳስቧል፡፡

በከተማዋ 76 ወንዞች ያሉ ሲሆን ሁሉም ለአካላዊ፣ ኬሚካላዊና ስነ-ህይወታዊ ብክለት የተጋለጡ መሆናቸውን ጥናቶች እንደሚያረጋግጡ ተመላክቷል።

ለዚህም የከተማ አስተዳደሩ ንፁህ ወንዝና ጤናማ አካባቢ እንዲፈጠር ደንቡን ተግባራዊ አድርጓል።

በአንዋር አህመድ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review