በአዲስ አበባ የደንብ ጥሰትን በ64 በመቶ መቀነስ ተችሏል- የደንብ ማስከበር ባለስልጣን

You are currently viewing በአዲስ አበባ የደንብ ጥሰትን በ64 በመቶ መቀነስ ተችሏል- የደንብ ማስከበር ባለስልጣን

AMN-ሚያዝያ 8/2017 ዓ.ም

አዲስ አበባን የደንብ ጥሰት የቀነሰባት ከተማ ለማድረግ በተሰራው ስራ የደንብ ጥሰት በ64 በመቶ መቀነስ መቻሉን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ገለጸ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የ2017 በጀት ዓመት የ9 ወራት እቅድ አፈጻጸሙን የክፍለ ከተማ እና የወረዳ አመራሮች በተገኙበት እየገመገመ ይገኛል።

የአዲስ አበባ ከተማ የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ፣ የደንብ ማስከበር የዘጠኝ ወራት አፈጻጸም የላቀ ውጤት የተመዘገበበት መሆኑን ተናግረዋል፡፡

አዲስ አበባን የደንብ መተላለፍ የቀነሰባት ከተማ ለማድረግ በተሰራው ስራም የደንብ ጥሰት በ64 በመቶ መቀነስ ተችሏል ብለዋል።

ባለስልጣኑ ከተቋም ግንባታ ጀምሮ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝም አመላክተዋል።

በመሀመድኑር አሊ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review