በአፍሪካ ህብረት ጉባኤ የተሳተፉ መሪዎች ወደ ሀገራቸው መመለስ ጀመሩ

You are currently viewing በአፍሪካ ህብረት ጉባኤ የተሳተፉ መሪዎች ወደ ሀገራቸው መመለስ ጀመሩ

AMN – የካቲት 10/2017 ዓ.ም

በ38ኛው የአፍሪካ ኀብረት የመሪዎች ጉባኤ ላይ የተሳተፉ መሪዎች ወደ ሀገራቸው መመለስ ጀመሩ።

የአልጄሪያ ፕሬዚዳንት አብዱልመጅድ ተቡን፣ የሩዋንዳ ፕሬዚዳንት ፓል ካጋሜ ፣ የፍልስጤም ፕሬዚዳንት መሐሙድ አባስ ፣ የባርባዶስ ጠቅላይ ሚኒስትር ሚያ አሞር ሞተሊ እና የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎሳ እንዲሁም የዩጋንዳ ምክትል ፕሬዚዳንት በአዲስ አበባ የነበራቸውን ቆይታ አጠናቀው መመለሳቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ለመሪዎቹ የመንግስት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በቦሌ አለምአቀፍ አየር ማረፊያ የክብር አሸኛኘት ማድረጋቸውም ተመላክቷል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review