በአፍሪካ ኀብረት ጉባኤ የተሳተፉ መሪዎች ወደ ሃገራቸው በመመለስ ላይ ናቸው

You are currently viewing በአፍሪካ ኀብረት ጉባኤ የተሳተፉ መሪዎች ወደ ሃገራቸው በመመለስ ላይ ናቸው

AMN – የካቲት 10/2017 ዓ.ም

በ38ኛው የኀብረቱ አመታዊ የመሪዎች ጉባኤ የተካፈሉ መሪዎች እና የመንግስታት ተወካዮች ወደ ሀገራቸው በመመለስ ላይ ናቸው ።

የደቡብ ሱዳን ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ሳልቫ ኬር ማያር ዴት ፣ የሴኔጋል ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ባሲሩ ዲዮማዬ ፋዬ፣ የማዳጋስካር ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት አንድሬ ራጆሊና ፣ የዚምባቡዌ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ኤምርሰን ምናንጋግ እና የጊኒ ቢሳው ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ኡማሮ ሲሶኮ ሙባሎ እና የሴኔጋል ፕሬዝዳንት ወደ ሀገራቸው መመለሳቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review