በአፍሪካ ዞን የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ሴራ ሊዮን ስታሸንፍ ኬንያ ነጥብ ጣለች

You are currently viewing በአፍሪካ ዞን የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ሴራ ሊዮን ስታሸንፍ ኬንያ ነጥብ ጣለች

AMN-መጋቢት 12/2017 ዓ.ም

ለ2026ቱ የዓለም ዋንጫ የአፍሪካ ዞን የማጣሪያ ጨዋታዎች እየተደረጉ ነው፡፡

በኢትዮጵያ ምድብ የምትገኘው ሴራ ሊዮን ጊኒ ቢሳውን 3ለ1 ያሸነፈች ሲሆን፣ በዚህም ነጥቧን ስምንት አድርሳ ወደ ሁለተኛ ደረጃ ከፍ ብላለች፡፡

የምስራቅ አፍሪካዋ ኬንያ በበኩሏ ከጋምቢያ ጋር 3ለ3 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይታለች፡፡

አንጋፋው ማይክል ኦሉንጋ፣ ባጃቤር እና ዊልሰን የኬንያን ግቦች ያስቆጠሩ ተጨዋቾች ናቸው፡፡

የቦሎኛ የቀድሞ አጥቂ ሙሳ ባሮው የጋምቢያን ሁለት ግቦች ሲያስቆጥር፣ የብራይተኑ ያንኩባ ሚንተህ ቀሪዋን ግብ በስሙ አስመዝግቧል፡፡

በቤኒ ማካርቲ የምትሰለጥነው ኬንያ ትናንት አቻ በመለያየቷ በ6 ነጥብ አራተኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ችላለች፡፡

እዚሁ ምድብ ላይ የምትገኘው ጋቦን ሲሸልስን 3ለ0 አሸንፋ መሪነቱን ከአይቮሪኮስት ተረክባለች፡፡

በሌሎች የትናንት ውጤቶች ሞዛምቢክ ኡጋንዳን 3ለ1፣ ዚምባብዌ ከቤኒን 2ለ2፣ ኬፕቨርዴ ሞሪሺየስን 1ለ0፣ ማላዊ በናምቢያ 1ለ0 እንዲሁም ሊቢያ ከአንጎላ 1ለ1 ተለያይዋል፡፡

የአፍሪካ ዞን የማጣሪያ ጨዋታዎች ዛሬም ሲቀጥሉ ቦትስዋና ከአልጄሪያ፣ ኢኳቶሪያል ጊኒ ከሳኦ ቶሜና ፕሪንስፔ፣ ቡርኪና ፋሶ ከጂቡቲ፣ ዲሞክራቲክ ኮንጎ ከደቡብ ሱዳን፣ ሩዋንዳ ከናይጄሪያ፣ ደቡብ አፍሪካ ከሌሴቶ፣ ጋና ከቻድ እና ብሩንዲ ከአይቮሪኮስት ጨዋታቸውን የሚያደርጉ ይሆናል፡፡

በታምራት አበራ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review