በኢስታንቡል በሬክተር ስኬል 6 ነጥብ 2 የተመዘገበ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ ተከሰተ

You are currently viewing በኢስታንቡል በሬክተር ስኬል 6 ነጥብ 2 የተመዘገበ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ ተከሰተ

AMN – ሚያዝያ 15/2017 ዓ.ም

በቱርኪዬ ኢስታንቡል በሬክተር ስኬል 6 ነጥብ 2 የተመዘገበ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ ተከስቷል።

ዛሬ ቀትር ላይ በተከሰተው በዚህ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ የኢስታንቡል እና ጎረቤት አካባቢ ነዋሪዎች በፍርሃት የመኖሪያ ህንጻቸውን ለቀው እንዲወጡ እንዳደረጋቸው የአናዶሉ የዜና ወኪል ዘግቧል፡፡

ይህ በዚህ እንዳለ ዛሬ ረፋዱ ላይ በኢስታምቡል አቅራቢያ የባህር ዳርቻ ቡዩኪክሚ በተባለ ስፍራ ላይ በሬክተር ስኬል 4 ነጥብ 9 የተመዘገበ የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱን የዜና ወኪሉ የሃገሪቱን የድንገተኛ አደጋ መቆጣጠር ባለስልጣን ጠቅሶ ዘግቧል።

ሆኖም ግን በአደጋው ምንም የተመዘገበ ጉዳት እንዳልደረሰ ተመላክቷል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review