በኢትዮጵያ ታሪክ ትልቁ የቡና ኤክስፖርት አፈጻጸም ተመዘገበ

AMN ግንቦት 06/2017

በበጀት ዓመቱ 10 ወራት በኢትዮጵያ ታሪክ ትልቁ የቡና ኤክስፖርት አፈጻጸም መመዝገቡን የኢትዮጵያ ቡና እና ሻይ ባለስልጣን አስታውቋል፡፡

ሀገሪቱ በ10 ወራት ውስጥ ከቡናብቻ ከ1 ነጥብ 8 ቢሊየን የአሜሪካን

ዶላር ላይ ገቢ ማግኘቷንም የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አዱኛ ደበላ (ዶ/ር) ገልጸዋል፡፡

ዋና ዳይሬክተሩ ባለስልጣኑ በበጀት ዓመቱ 10 ወራት 354 ሺህ 302 ቶን ቡና ወደ ውጭ መላኩን ጠቁመዋል፡፡

ይህም ከባለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በመጠን የ145 ሺህ 316 ሺህ ቶን፣ በገቢ ደግሞ የ869 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ጭማሪ እንዳለው አስታውቀዋል፡፡

በ10 ወራት የኢትየጵያ ቡና ቀዳሚ መዳረሻ ሀገራትም በቅደም ተከተል ጀርመን፣ ሳዑዲ አረቢያ እናአሜሪካ እንደነበሩም አስታውሰዋል፡፡

ለተመዘገበው ስኬት ከመንግስት ጋር በቅንጅት ርብርብ ላደረጉ አካላትም ዋና ዳይሬክተሩ ምስጋና ማቅረባቸውን ከባለስልጣኑ የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review