በኢትዮጵያ እና በቱርኪዩ መካከል ያለውን ጠንካራ የሁለትዮሽ ግንኙነት ማላቅ ይገባል -አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ

You are currently viewing በኢትዮጵያ እና በቱርኪዩ መካከል ያለውን ጠንካራ የሁለትዮሽ ግንኙነት ማላቅ ይገባል -አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ

AMN- ጥር 1/ 2017 ዓ.ም

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ በኢትዮጵያ የቱርኪዩ አምባሳደር በርክ ባራን ጋር ተወያይተዋል።

በውይይታቸው የንግድና ኢንቨስትመንት ትስስሮችን ማሳደግ እንዲሁም በአፍሪካ ቀንድ ሰላምና ደህንነት ላይ ያለውን ትብብር ማጠናከር ጨምሮ በሁለትዮሽ፣ቀጠናዊ እና ባለብዙ ወገን ዲፕሎማሲ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል።

አምባሳደር ምስጋኑ በኢትዮጵያ እና በቱርኪዩ መካከል ያለውን ጠንካራ የሁለትዮሽ ግንኙነት አጽንኦት ሰጥተው በንግድ እና ኢንቨስትመንት ላይ ያላቸውን ግንኙነት የበለጠ ማላቅ እንደሚገባ አስረድተዋል።

የቱርኪዩ ኩባንያዎች እና ባለሃብቶች በሀገሪቱ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየተደረጉ ካሉት የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያዎች በመነሳት በኢንቨስትመንት ዘርፎች እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርበዋል ።

አምባሳደር ምስጋኑ በኢትዮጵያ እና ሶማሊያ መካከል የተፈረመውን ስምምነት በተሳካ ሁኔታ እውን እንዲሆን ለተደረገው ጥረት ለቱርኪዩ ህዝብ እና መንግስት ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

አምባሳደር ባራን በአንካራ ስምምነት የኢትዮጵያ እና የሶማሊያ መንግስታት የገቡትን ቃል በማድነቅ በቆይታቸው ዘርፈ ብዙ ግንኙነቶችን ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ ያላቸውን ቁርጠኝነት መግለፃቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review