በኢትዮጵያ የጀርመን አምባሳደር ጄንስ ሀኔፌልድ የዓድዋ ድል መታሰቢያን ጎበኙ

You are currently viewing በኢትዮጵያ የጀርመን አምባሳደር ጄንስ ሀኔፌልድ የዓድዋ ድል መታሰቢያን ጎበኙ

AMN – ሚያዝያ 15/2017 ዓ.ም

በኢትዮጵያ የጀርመን አምባሳደር የሆኑትን ጄንስ ሀኔፌልድ የዓድዋ ድል መታሰቢያን ጎብኝተዋል፡፡

አምባሳደሩ ወደ ዓድዋ ድል መታሰቢያ በመጡበት ወቅትም የመታሰቢያዉ ዋና ዳይሬክተር አቶ ግሩም ግርማ እና ሌሎች የማኔጅመንት አባላት አቀባበል አድርገዉላቸዋል፡፡

አምባሳደሩም በዓድዋ ድል ጉብኝት ማድረጋቸው እጅግ እንዳስደሰታቸው እና ወደፊት አብሮ ለመስራት እንደሚፈልጉ ገልጸዋል፡፡

የመታሰቢያዉ ዋና ዳይሬክተር አቶ ግሩም ግርማ፤ ጀርመን በቴክኖሎጂ ሽግግርና በተለያዩ የልማት ሥራዎች እያደረገች ላለችው ከፍተኛ ድጋፍ አመስግነዋል፡፡

ወደፊት በቴክኖሎጂ እና በተለያዩ መስኮች ከመታሰቢያዉ ጋር አብረው እንዲሰሩ እና በተለይም በሙዚየም ዘርፍ ጀርመን ያላትን ልምድ በማካፈል እገዛ እንዲያደርጉ መጠየቃቸውን ከመታሰቢያው ማኅበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review