የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ 4ኛ ኮርስ አዲስ ምልምል የሰላም ሰራዊት አባላት የተግባር እና የንድፈ ሀሳብ ስልጠና በሁሉም ክፍለ ከተሞች አስጀመረ።
በመድረኩ የአዲስአበባ ከተማ የሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ፣ በከተማዋ አስተማማኝ እና ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ የሰላም ሰራዊቱ ሚናውን እየተወጣ ይገኛል ብለዋል።
በከተማዋ የወንጀል ምጣኔን በመቀነስ አንፃር ሰፊ ስራዎች መሰራታቸውን የተናገሩት ኃላፊዋ፣ ይህ ተግባር በቀጣይም ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።
የተጀመረው ስልጠና በስኬት ተጠናቆ አላማና ግቡን እንዲመታ ድጋፍና ክትትልን በማጠናከር ለልማትና አብሮነት እንቅፋት የሆኑ ተግዳሮቶችን በጋራ ለመሻገር ትልቅ አደራና ታሪካዊ ኃላፊነት የተጣለበት ስለመሆኑም ተናግረዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ሚደቅሳ ከበደ በበኩላቸው፣ የሰላም ሰራዊት የህዝቡን ደህንነት በቁርጠኝነት ለመጠበቅ፣አብሮነትን ለማጽናት፣ የልማቱን ቀጣይነት ለማረጋገጥ ያላቸውን ፍላጎት የሚያሳይ በመሆኑ የሰላም አምሳደሮች በመሆናቸው ሊኮሩ እንደሚገባ ተናግረዋል።
የስልጠናው ተሳታፊዎችም የሚወስዱትን ስልጠና ወደ ተግባር በመቀየር ለሰላም ዘብ ለመሆን ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል።
ስልጠናው በሁሉም ክፍለ ከተሞች ከ11 ሺህ በላይ ለሚሆኑ አዲስ ምልምል የሰላም ስራዊት ሰልጣኞች በንድፈ ሀሳብና በተግባር ታግዞ ለ10 ቀናት እንደሚሰጥ ተመላክቷል።
በመሀመድኑር አሊ





See insights and ads
All reactions:
4343