በከተማዋ የተከናወኑ የልማት ስራዎች ግባቸውን እንዲያሳኩ ባለድርሻ አካላት ኃላፊነታቸዉን መወጣት ይገባቸዋል- ወንድሙ ሴታ (ኢ/ር)

You are currently viewing በከተማዋ የተከናወኑ የልማት ስራዎች ግባቸውን እንዲያሳኩ ባለድርሻ አካላት ኃላፊነታቸዉን መወጣት ይገባቸዋል- ወንድሙ ሴታ (ኢ/ር)

AMN- መጋቢት 26/2017 ዓ.ም

በከተማዋ የተከናወኑ የልማት ስራዎች የታለመላቸዉን አላማ እንዲያሳኩ እና ለትዉልድ እንዲተላለፉ ባለድርሻ አካላት እና ተጽእኖ ፈጣሪ ግለሰቦች ኃላፊነታቸዉን መወጣት እንደሚገባቸዉ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ወንድሙ ሴታ (ኢ/ር) ተናገሩ::

የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽሕፈት ቤት በማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ዙሪያ የባለድርሻ አካላትን ግንዛቤና ተሳትፎ ለማጎልበት የሚያስችል ውይይት እያካሄደ ነው ::

በመርሐ-ግብሩ የከተማዋ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ፣ የሃይማኖት አባቶች ፣ የሚዲያ የስራ ኃላፊዎች፣ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎችን ጨምሮ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተሳትፈዋል ::

በመድረኩ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ወንድሙ ሴታ (ኢ/ር) ባለፉት ጊዚያት የተከናወኑ የልማት ስራዎችን ሪፖርት አቅርበዋል፡፡

በሪፖርታቸውም የከተማዋን ገፅታ የቀየሩ እና የህዝብን ጥቅም ያረጋገጡ በርካታ ተግባራት መከናወናቸውን አመላክተዋል ::

በከተማዋ የተከናወኑ የልማት ስራዎች ለትውልድ እንዲተላለፉ ባለድርሻ አካላት ተፅእኖ ፈጣሪ ግለሰቦች፣ እና ህብረተሰቡ ኃላፊነታቸዉን መወጣት እንሚገባቸውም አስገንዝበዋል::

የተከናወኑ የልማት ስራዎች የታለመላቸዉን አላማ እንዲያሳኩ ለብረተስቡ ግንዛቤ በመፍጠር ረገድ የሃይማኖት አባቶች እና የኪነ ጥበበ ባለሙያዎች ሰፊ ሚና እንዳላቸውም አንስተዋል፡፡

በቴዎድሮስ ይሳ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review